የቤት እመቤት



“ከልጅ ጋር ከባድ ነው”

እናቶች በልጅ ማሳደግ ጊዜ ውስጥ ስለ ማህበራዊ ህይወት ተሳትፎቸው ወይም ስለ ሥራቸው አልያም ሰለሌሎች ሊያከናውንኗቸው ይችሉ የነበሩ፤ በመውለዳቸው ምክንያት ያቋርጧቸውን ነገሮች በተመለከት ሲጠየቁ “ከልጅ ጋር ከባድ ነው” ሲሉ ይደመጣሉ።
በእርግጥ ልጅ ከተወለደ በኋላ እንደቀድሞው ነገሮችን መከውን ይከብዳል። ቢሆንም “አይቻልም” ብሎ መደምደም ግን አይገባም።
ይቻላል?
ከልጅ ጋር ሆኖ መስራት፣ መማር፣ አዲስ ነገር መፍጠር ይቻላል።
ለዚህ የሚያስፈልገው ነገር እንደሚቻል ማመን ነው።
ቀጥሎ ደግሞ
1. ምን መሰራት እንደሚቻል እና እንደማይቻል ማወቅ ። ይህ እንድ እናቲቱ የኑሮ ሁኔታ፣ ፍላጎት እና አቅም ይወሰናል
2. ልጆቻችንን የምንመግብበት፣ የምናጫውትበት፣ የምናጥብበት፣ የምናስተምርበት፣ የምናስተኛበት ሰአት የታወቀ እና መደበኛ ማድረግ።
3. ልጆ የሚነገራቸውን ይሰማሉ። ስለዚህ “የጨዋታ ጊዜ ነው፣ የምግብ ጊዜ ነው፣ የመኝታ፣ የፅዳት እያሉ እየነገሩ በፕሮግራም እንዲመሩ ማድርግ። በእነዚህ ጊዜያት አንዱን ካንዱ ሳይቀላቀሉ መፈፅም። ልጆቹም የሚያዩትን ይዘው ስለሚያድጉ እናት ቤት ውስጥ የምታድርገውን ማንኛውንም አይነት ስራ በቀላሉ መከወን ትችላለች።
የአራት ልጆች እናት ነኝ። የመጀመሪያውን “ሁለት ሦስት መልክ” መጽሐፍ ስጽፍ የመጀመሪያ ልጄን ነፍሰጡር ነበርኩ። መጽሐፋ የተጠናቀቀው ሁለተኛዋ ልጄ ተወልዳ ሁለት አመት ተኩል ሲሆናት ነው።
fb_img_1526550307727
የሚስፈልጋቸውን በሰአቱ ከከውንኩ በኋላ ቀንና ማታ በሚተኙበት ጊዜ እንዲሁም ከተነሱ በኋላ አጠገባቸው ቁጭ ብዬ ሲጫወቱ እየጠብኩ። እጽፋለሁ። በዚህ ጊዜ ላፕቶፔን መምታት ወይም ሌላ አይነት ረብሻ ሲያደርጉ “ይሄ የማማ የሥራ ስአት ነው” እያልኩ ደጋግሜ እነግራቸዋለሁ። በዚህ ምክንያት ኮምፒውተር ላይ ስቀመጥ ” ማማ ስራ ነው? ” እያሉ ከመጠየቅ ውጭ ወደ እኔ አይመጡም። የትኛውንም አይነት ነገር ስከውን እየነገርኳቸው ነው። ስለዚህ አንዱን ከአንዱ ሲቀላቅሉ ካየኋቸው ” አሁን የምን ሰአት ነው?” በማለት እጥይቃቸውና በሰአቱ የሚደረገውን እንዲያደርጉ እመራቸዋለሁ።
“ልጅና ውሃ…” እንደሚባለው እኛ ባሳየናቸው መንገድ ነውና የሚጓዙት፤ አስተካክለን በመምራት ለአላማችን መሳካት ደጋፊ እንጂ መስናክል እንዳይሆኑ ማድረግ ይቻላል።

No comments:

Post a Comment