Friday, December 13, 2019

ከእኔ የተሻሉ



በአገራችን ተደማጭ የሆነው የሸገር ጨዋታ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መአዛ ያለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 3ዐ/ 2ዐዐ8 አርቲስት ሀመልማልን እንግዳ አድርጋ አቅርባት ነበር፡፡
ለሀመልማል እናቷን በተመለከተ ከመአዛ ለቀረበላት ጥያቄ ምላሽ እየሰጠች እንዲህ አለች እናቴ ለእኔ እሷ ያለገኝችውን ነገር ሁሉ ለእኔ አድርጋልኛለች፣ የእሷን ፍላጎት ትታ የእኔን ለማሟላት ለፍታለች፤ እኔም ራሴን ከቻልኩ በኋላ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ለማድረግ ጥሬያለሁ፡፡ እናቴ ለእኔ እንደሆነችው ሁሉ እኔም ለልጆቼ ከእኔ የተሻለ ነገር እንዲያገኙ ከእኔ የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ለፍቻለሁ አለች ፡፡

ይህ በአብዛኛው እናቶች ዘንድ እውነት የሆነ ነው፡፡ እናቶቻችን እነሱ መማር እየፈለጉ እኛን ሲያስተምሩ፣ እነሱ መልበስ እያማራቸው እኛን ሲለብሱ፣ እነሱ እያራበቸው እኛን ሲያጠግቡ፣ እኛን ከፍ ከፍ እያደረጉ እነሱ ግን ዝቅ ቅዝ ሲሉ አይተናል፡፡
እኛስ የአሁን ዘመን እናቶች በእውነት ይህን መስዋእትነት ለልጆቻችን ለመክፈል ዝግጁዎች ነን?
እኔ በበኩሌ እናቴ እንዴት አድርጋ አምስት ልጅ ሲደመር የሙሉ ቀን አስተማሪነትን ይዛ እዚህ እንደደረሰች እና እኛንም እዚህ እንዳደረሰች ሳስብ በን ምትሀት ነው እላለሁ፡፡ በዚህ አጭር የእናትነት ጊዜዬ የተማረርኩባቸው፣ የደከምኩባቸው፣ ያዘንኩባቸው፣ ተስፋ የቆረጥኩባቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው፡፡ ልጆቼን ያማረርኩበትም ቀን እንደዛው፡፡

የእናቶቻችንን ጥንካሬ፣ ቆራጥነት፣ ተስፋ፣ አላማ፣ ብርታት፣ እምነት፣ ቻይነት፣ እና ትንሽ አምላክነት ይኖረን ዘንድ ለእኛ ለዚህ ትውልድ እናቶች እመኛለሁ፡፡

እናቶቻች እኛን ከእነሱ እንድንሻል አድርገው አሳድገውናል፣ እኛም ልጆቻችን ከእኛ የበለጡ አድርገን የማሳደግ ግዴታ አለብን፡፡ ይህን ማድረግ ካልቻልን ግን የትውልዱ ክስረት በእኛ ራስ ላይ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን

/ሮዝ መስቲካ/

ስነ ምግባርና ቅጣት


ከልጆች አመጋገብ ጋር ለተነሱ ጥያቄዎች በምቹ ቤት የተሰጡ መልሶች።
***ምግብ የማይወዱ ልጆችን በተመለከት
***ለሌት ህጻናት ምን ያህል ጡጦ መጥባት አለባቸው?
እና ሌሎችም።
ምስሉን ይመልከቱት

"ሚስትህን ማስተዳደር ያቅትሃል?

ወንድ ልጁን ሲድር "ሚስትህን ማስተዳደር ያቅትሃል? ለምን ትሰራለች? አስቀምጣት" ያለ አባት
ሴት ልጁን ሲድር "ስራሽን እንዳታቆሚ! የእሱ እጅ ጠባቂ እንዳትሆኚ ይላል።"

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!


 
ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!
በየተቋማቱ የህጻናት ማቆያ ለማዘጋጀት:-
ማሰብ
ማስተባበር/መተባበር
መተግበር

ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ

ይህ ዘመቻ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ እጅግ ብዙ በእኔ አቅም ሊፈቱ የማይችሉ የሠራተኛ እናቶችን ችግር እሰማለሁ።
ከዚህ በታች የተቀመጠው መልእክትም በኢትዮጵያ አየር መንገድ የምትሠራ አዲስ እናት መልእክትን ነው።
ከወለደች ሦስት ወር ሊሆናት ነው። የሦስት ወር ህጻን አስቀምጣ ወደ ሥራ ልትመለስ ነው። ይህ ሥራ እንደሌሎቹ ሥራዎች ማታ ወደ ቤት የሚመለሱበት አይደለም። ከአገር የሚስ
ያስወጣ አውሎ የሚያሳደር እንጂ።
እስቲ አስቡት።
መልእክቱን ሼር እንድታደርጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ!
"I am working in Ethiopian in the position of cabin crew. I am already gave birth for my second baby before 45 days. In this case my maternity leave will be done after 15 days. After that they will allow one month with out pay. And they r expecting me to start flight when my baby is only three month 😱. In z previous times 3 month leave without pay was allowed. But currently they deny our request. In our case once we start flight, let alone breastfeeding, seeing our babies is restrictred. I am so stressed leaving my baby in such a way."

ጡት ማጥባት

ለኣዲስ እናቶች አስቸጋሪ አና ፈታኝ ክሆኑ ጉዳዮች አንዱ ጡት ማጥባት ነው። ጡት ማጥባት የሚጠይቀው በቁጥር የበዙ ነገር ግን ቀላል የሆኑ ጉዳዮች አሉ። እነዚህን ጉዳዮች ካለማስተዋል እና ካለመተግበር የተነሳ ብዙ እናቶች ጡት ሳያጠቡ ይቀራሉ። አንደኛውና ብዙ እናቶች የሚገጥማቸው ችግር የጡጥ ወተት ማነስ ነው። ይህ የጡት ወተት ማነስ በአርግጥም አንሶ ሊሆን ይችላል። አለዚያም የእናቶቹ ግምት ይሆናል። ሁለቱንም ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉና እናቶች በቀላሉ በቂ የሆነ ወተት እንዲኖራቸው የሚያደርግ መላ እነሆ፡- ጭንቀትን ማስወገድ በበቂ ሁኔታ መመገብ አና መጠጣት በቂ እረፍት ማድረግ ቶሎ ቶሎ ማጥባት የትዳር አጋርና የቤተሰብ ድጋፍ እነዚህ መሠርታዊና በቂ የጡት ወተት ለማግኘት የሚረዱ ዘዴዎች ናቸው።https://ethiopianmothers.wordpress.com/…/%e1%8b%a8%e1%8c%a…/

"ለውጥ እንደዋዛ አይመጣ። እንደዋዛ ግን ይጀመራል።"

"ለውጥ እንደዋዛ አይመጣ። እንደዋዛ ግን ይጀመራል።"
በዚህ መሪ ቃል የተጀመረው "የተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ" ዘመቻ ሦስተኛ አመቱ ላይ ደርሷል
በጥቂቱም ቢሆን ለውጦችን አይተናል።

ትብብራችሁን እፈልጋለሁ።

ጤና ይስጥልኝ !
ትብብራችሁን እፈልጋለሁ።
በወሊድ ምክንያት ምን ያህል ሴቶች ሥራ እንዳቆሙ ሊያሳይ የሚችል መረጃ ለማሰባሰብ ጥረት እያደርኩ ነው።
ለዚህ መረጃ አሰባሰብ ሊረዳኝ እንዲችል #ለልጄ የሚል ሀሽ ታግ አዘጋጅቻለሁ።
ስለዚህ ሥራ የለቀቃችሁ እናቶች ወይም ሚስቶቻችሁ ሥራ የለቀቁ ባሎች #ለልጄ የሚለውን ሀሽ ታግ በአስተያየት መስጫው ላይ እንድታስቀምጡልኝ እንዲሁም የምትኖሩበትን ከተማ በመጨመር እንድትተባበሩኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ ።
#ለልጄ አዲስ አበባ
በአካባቢያችሁም ሥራ ያቆመች እናት ታውቁ እንደሆነ
#ለልጄ አዲስ አበባ 1
በማለት እንድትገልፁልኝ ይሁን።
ስለ ጊዜያችሁ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ
Share. Share. Share. Share

"ኮሽ"

"ኮሽ" ባለ ቁጥር ሴቶች ከስራ ገበታቸው እንዳይቀሩ፣
የቤት ሠራተኛ በጠፋ ቁጥር የአለቃቸውን ፊት እንዳያዩ ለማድረግ፤
እውነቴን ነው!

የእሷ ደመወዝ

የእሷ ደመወዝ 5,000 (ምናምኑ ሳይቀናነስ)
የባሏ ደመወዝ (አይታወቅም) ለቤት ወጭ በወር ሁለት ሺህ ብር ይሰጣል።
እሷ ለቤት ሠራተኛ 1500 ትከፍላለች።
*** የቤት ኪራይ 5000
*** የአራት ወር ልጇ የዱቄት ወተት እና የዳይፐር ወጭ በየሳምንቱ አለ

ሮዝ መስቲካ፡ 'ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ ለእናቶች' ስትል የምትወተውተዋ እናት (ቢቢሲ)

ሮዝ መስቲካ፡ 'ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ ለእናቶች' ስትል የምትወተውተዋ እናት


ሮዝ ከልጇ ጋርImage copyrightROSE MESTIKA

ዓለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው። የእናት ጡት ወተት ለልጆች ጤናማ አካላዊና አዕምሯዊ እድገት ወሳኝና መተኪያ የሌለው ነው። ለዚህም ነው እናቶች ልጆቻቸውን ያለ ተጨማሪ ምግብ እስከ ስድስት ወር ድረስ ከዚያም ከተጨማሪ ምግብ ጋር እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲያጠቡ የሚመከረው።
ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ይህንን መተግበር አዳጋች ሲሆን ይስተዋላል።
ልጆችን ጡት ማጥባት ሳይንስ ነው። ከእናትየዋ አመጋገብ ጀምሮ (የምግብ አሠራር በሉት) ቀላል አይደለም። አቀማመጡ፣ የልጅ አስተቃቀፉ፣ የጡት አጎራረሱ በዘፈቀደ የሚደረግ አይደለም።
መራመድ ቢፈልጉም ለረዥም ሰዓት ለመቀመጥ ይገደዳሉ። እጅ ይዝላል። ፍላጎት ባይኖርም መመገብ ይጠይቃል፤ ያገኙትን አሊያም ያሻዎትን ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ። አጣደፊ ጉዳይ ቢገጥመዎት ጡትዎን ከልጅዎ አፍ መንጠቅ ያሳሳል። ግራኝ ሆኑም ቀኝ በሁለቱም ክንድዎ ልጅዎን ማቀፍ ግድ ይላል- ሁለቱንም ጡቶች ማጥባት ስላለብዎ።
ያስርባል፤ ልብ ያዝላል። ያጠቡትን የጡት ወተት መጠንን የመስፈሪያ መንገድ ስለሌለ ልጅዎ ምን ያህል የጡት ወተት እንዳገኘ በቀላሉ ለማወቅ ስለማይቻል ያስጨንቃል።
ለእናት ከባዱ ነገር ደግሞ ልጀ አልጠገበም ብሎ ማሰብ ነው። አንዳንዴም የጠቡት ይወጣና ለንዴት ይዳርግዎት ይሆናል። ወተት አግቷል አላጋተም ጡትዎን የሚዳብሱበት ቁጥር ይበረክታል።
ጠብተው ሲጨርሱም ቆሞ ማስገሳት አለ። በተለይ ለጀማሪ እናቶች አሳሩ ብዙ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የትዳር አጋሮች ድርሻቸውን ካልተወጡ ፈተናው ያይላል- ጡት ወደ ማስጣል ውሳኔም ሊያደርስ ይችላል። ይህን ያለችን ሮዝ መስቲካ ናት።
በማስ ኮሚዩኒኬሽን የመጀመሪያ ድግሪ አላት። በተለያዩ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግላለች። በሚዲያው ዘርፍም በጋዜጦችና በራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ ሠርታለች።
'ሁለት ሦስት መልክ - ልጅ ወልዶ ማሳደግ' የሚል መፅሐፍ አላት። መጽሐፉ ከእርግዝና ጀምሮ ልጆችን በማሳደግ ሂደት የገጠሟትን ፈተናዎች እና የሌሎች እናቶች ተሞክሮ ተካቶበታል።
ሮዝ መስቲካ 'ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ ለእናቶች' በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች በምታደርገው ዘመቻዎቿና ቅስቀሳዎቿ ትታወቃለች።
ባለትዳርና የአራት ልጆች እናት ናት።
ከመጀመሪያ ልጇ በስተቀር ሦስቱን ልጆቿን ለተከታታይ ስድስት ወራት ያለተጨማሪ ምግብ አጥብታለች።
የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ በልምድ ከምታውቀው ውጪ የተሻለ ግንዛቤ ስላልነበራት እና የወለደችበት የጤና ተቋም ልጇ እንደተወለደ እንገር በመስጠት ፋንታ የዱቄት ወተት ስለሰጡት ጡት መጥባት አሻፈረኝ ብሎ እንደቀረ ምክንያቱን ትናገራለች።
እግረ መንገዷን ኃላፊነታቸውን በሚገባ የማይወጡ የጤና ተቋማትን በመኮነን ነው ታዲያ።
በዚህ ጡት ባልጠባው ልጇና በሌሎቹ መካከል በሽታን በመቋቋም ረገድ ልዩነቱ ከፍተኛ መሆኑን አስተውላለች። እርሱ በቀላሉ በጉንፋንም ሆነ በትንሽ በሽታ ይዳከማል፤ ሌሎቹ ግን በሽታን የመቋቋም አቅማቸው የተሻለ ነው።
በወሬ መሃል ሳይጠባ ማደጉን ሲሰማም 'ለምን?' ብሎ ይጠይቃታል፤ ይናደዳል። እርሷም በእርሱ ፊት እንዲህ ብላ ማውራት ትታለች።
ሮዝ፤ ልጆቿን እንደ እርሷ ሆኖ የሚንከባከብ ሰው ስለሌለ የመጀመሪያ ልጇን እንደወለደች ከባለቤቷ ጋር ተማክራ ሥራዋን ትታ ልጆቿን በማሳደግ ተጠምዳ ትውላለች። ምን አልባት አማራጮች ቢኖሩ፣ የወሊድ ፈቃድ ጊዜው ቢጨመር፣ ሥራ ቦታዎች የሕፃናት ማቆያ ቢኖር ወደ ሥራዋ ተመልሳ መድረስ የምትፈልግበት ቦታ ልትደርስ ትችል እንደነበር ታስባለች።

ሮዝ ልጇን ስታጠባImage copyrightROSE MESTIKA

ልክ እንደሷ ሁሉ አገራቸው የምትፈልጋቸው፣ ችሎታና አቅም ያላቸው ሴቶች እየተቆጩ በየቤታቸው ቀርተዋል ትላለች። ሩቅ ሳትሄድ እናቷ እርሷን ለማሳደግ ሲሉ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን ዋቢ ታደርጋለች።
"ከልጅነቴ ጀምሮ የሴቶች ኑሮ በጣም ያሳዝነኛል፤ ያሳስበኛል። እናቴ መምህር ስለነበረች የከፈለችውን ዋጋ አውቃለሁ። ቀኑን ሙሉ ታስተምራለች፤ ቤት ውስጥ ደግሞ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ ኃላፊነቶች ተወጥራ ትውላለች። በዚህም ሴቶች ያሉባቸውን ችግሮች እያየሁ ነው ያደኩት" ትላለች።
በዚህም ተነሳስታ በ1996 ዓ.ም የሴቶች ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያተኩር 'አብነት' የተባለ መጽሔት ጀምራ ነበር።
እርሷ እንደምትለው በቂ ዝግጅት ሳታደርግ በመጀመሯና ገበያ ላይ የሚፈለገው ይዘት ታዋቂ ሰዎች ላይ ያተኮረ፣ ስሜታዊነት የሚንፀባረቅበት፣ የሴቶች ሕይወት ላይ ሳይሆን አካላዊ ቁንጅና ላይ ያተኮረ ስለነበር ገበያ ላይ እምብዛም አልቆየም።
ሴቶች ላይ የሚሰሩ ተቋማትም እንደዚህ ዓይነት ሥራዎችን የማበረታታትና የመደገፍ ልምዱ የላቸውም።
ያኔ ነው ስለሴቶች አብዝታ መቆርቆር የጀመረችው።
"ከባለቤቴ ድጋፍ በማግኘቴና ሥራዬን ለቅቄ ልጆቼን ማጥባት የቻልኩት እድለኛ ሆኜ ነው፤ ይህ እድል የሌላቸው እናቶችስ?" ጥያቄዋ ነው።
"ትዳር መያዝና ልጅ መውለድ ስኬታማነት እንደሆነ በማሰብ፤ ወግ ማዕረጉን እንጂ በውስጡ ያለውን ተግዳሮት በቀናነት የሚያካፍል የለም" ትላለች።
ሮዝ እንደምትለው የትዳር አጋር ጥሩ የገቢ ምንጭ ኖሮት ሥራ ትቶ ልጅ ማሳደግን መታደልና ደስታ ብቻ እንደሆነ ይቆጠራል። ይሁን እንጂ ሥራ ትቶ ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም። በአንድ ወቅት ድብርት ውስጥ ገብታ እንደነበር ታስታውሳለች - ሮዝ።
ምንም እንኳን ባለቤቷ ድርሻውን በመወጣቱ ፈተናዎቹን ማለፍ ብትችልም፤ ሥራ ትቶ ቤት ውስጥ መዋል በራሱ የሚያመጣውን ተፅእኖ እንዳለ በተግባር ተመልክታዋለች። ይህ በሌለበት ግን ቤተሰባዊና ማህበራዊ ቀውሶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ትናገራለች።
እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ዘመቻ ወደ ማካሄዱ እንዳዘነበለች ትናገራለች - ሮዝ መስቲካ።
እንዲህ ዓይነት ዘመቻዎችን ማካሄድ ከጀመረች አራት ዓመታትን አስቆጥራለች። በባለቤቷ ሥራ ምክንያት ወደ ህንድ አገር ተዛውረው ሳለ እዚያው ሆና ነው የጀመረችው። በማህበራዊ ሚዲያዎች በምታካሂዳቸው ዘመቻዎች እናቶች ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ እንዲያገኙና ያለ ተጨማሪ ምግብ ልጆቻቸውን ጡት እንዲያጠቡ ቅስቀሳዎችን ታደርጋለች።
ሮዝ ሐምሌ 27/2011 ዓ.ም የጡት ማጥባት ሳምንትን በማስመልከት በጁፒተር ሆቴል መሰናዶ አዘጋጅታለች። በዝግጅቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ፤ ለስድስት ወር ያህል ያለተጨማሪ ምግብ፤ ከስድስት ወር በኋላ ለሁለት ዓመታት ልጆቻቸውን ያጠቡ እናቶችን ይበረታታሉ። የሕፃናት ማቆያ ያላቸው መሥሪያ ቤቶች ይመሰገናሉ።
የግል ድርጅቶች ሆነው መንግሥት ከሚፈቅደው ውጪ የወሊድ ፈቃድ የጨመሩ ድርጅቶችም ምስጋና እንደሚቀርብላቸው ገልጻልናለች።

የሮዝ ያልተመለሱ ጥያቄዎች

ሴቶችንና ሕፃናትን የተመለከቱ ሕጎችን በዝርዝር ባትመለከተም የሚከተሉት ግን አሁንም ጥያቄዎቿ ናቸው።
• የወንዶች አጋርነት
• የወሊድ ፈቃድ የተከለከሉ እናቶች፤ እረፍት ወስደው ሲመለሱ ሥራቸውን ያጡ እናቶች ጉዳይ
• የህፃናት ማቆያ በየመሥሪያ ቤቱ እንዲቋቋም የሚያዘውን አዋጅ ትግበራ ክትትል
• እናቶች ልጆቻቸውን እስከ ስድስት ወር እንዲያጠቡ ለማድረግ ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የሚሉ
"ሁሉም ያሉት ፖሊሲዎች የሚተገበሩት ጤናማ ትውልድ ሲኖር ነው" የምትለው ሮዝ እናቶችና ሕፃናትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው ታሳስባለች።

Tuesday, January 1, 2019

ጠላት ቁጥር አንድ- ስልክ

በልጆች እና በወላጆች መካክል፣ በልጆች እና በጤናማ አስተዳደግ መካከል፣ በልጆች እና በማህበራዊ ህይወት መካከል ጣልቃ የገባው  ጠላት ስልክ ነው።
አካላዊ ቅጣት የሚታይ እና የሚዳሰስ ቢሆንም በሞባይል ስልክ እና በመሰሎቹ የሚደርሰው ጉዳት በወቅቱ የማይታይ እና የማይዳሰስ የአአምሮ እና የአካላዊ ጤና ጉዳት ነው።
ስልክ ልጆችን ያለምንም ገመድ አስሮ የሚያቀምጥ ነገር ነው። ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸው ሲሯሯጡ እና ሲረብሹ ስልክ በመስጠት ያስቀምጧቸዋል።

ማወቅ ያለብን፦ስልክም ሆነ ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ቴሌቪዝንን ጨምሮ ለልጆች አካላዊ እና ማህበራዊ ጤና ጠንቅ መሆናቸውን ነው።
ማውቅን ያለብን፦  በተለይ ከሶስት አመት በታች ላሉ ሕጻናት ስልክ በመስጠት ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ይበልጣል።
ማወቅ ያለብን፦ መቼ እና እንዴት መስጠት እንደሚገባ ነው።
ማወቅ ያለብን፦ ስልክም ሆነ ቴሌቪዝን ልጆችን ከወላጆች፣ ክማህበረሰቡ ይልቁንም ከራስቸው እንድሚያራርቃቸው ነው።
ማውቅ ያለብን፦ ስልክም ሆነ ቴሌቪዝን በአግባቡ ከተጠቀመንበት ጠቃሚ መሆኑን ነው።
ስልክ ለልጆች መቼ መሰጠት አለበት?
  1. ሆስፒታል- ለክትባትም ሆነ ለህክምና ልጆች ሲሄዱ በስልክ እንዲጫወቱ ማድረግ ለወላጅም ለልጅም እረፍት የሚስጥ ነገር ነው። ሆስፒታል ውስጥ ሲሯሯጡ ከሚመጣው ጭንቀት እና ረብሻ ይታደጋቸዋል።
  2. ለጉብኝት ወይም ዘመድ ጥየቃ ፦ በዚህ ጊዜ በተለይ ልጆች የሌሉበት እና ለእነሱ የሚሆን ነገር በሌለበት ቦታ ስልክ መስጠት ለወላጆችሁም ለልጆችም ጥቅም አለው። ወላጆች ጉዳያቸውን በእርጋታ ይጨርሳሉ። ልጆችም ሳይሰላቹ እና ሳይበሳጩ ይቆያሉ።
  3. ረዥም ጉዞ ሲያደርጉ፣
  4. እናት ወይም አባት የቤት ስራ በሚሰሩበት ጊዜ በተለይ ደግሞ ምግብ በሚያበስሉበት እና በሚያፀዱበት ጊዜ።
  5. በሰንበት ቀናት፣ በበአኣላት ወይም ልጆች ጥሩ ነገር ሲሰሩ እንድ ሽልማት።
ማውቅ ያለብን፦ ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ በተለይ ስልክ በቀን ከሁለት ሰአት በላይ እንዲጠቀሙ ማድረግ አደጋ አለው። አአምሯዊ ቅጣት ይሆናል